ኤቲኤም እና POS አገልግሎቶች

ኤቲኤም እና POS አገልግሎቶች

በዘመን ሒሳብ ሲከፈት ሁሉም ደንበኞች የኤቲኤም ካርድ እና የግል መለያ ቁጥር (ፒን) ያገኛሉ። ኤቲኤም በምቾትዎ ገንዘብ እንዲቀበሉ ይፈቅድልዎታል። እንዲሁም ቀሪ ሂሳብዎን እንዲመለከቱና ገንዘብ እንዲያስተላልፉ ያስችልዎታል። “Z Tap” አሁን ሁሉም የዘመን POS ማሽኖችና አብዛኛዎቹ ኤቲኤሞች ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ወጥቶባቸው በዘመናዊ መንገድ የቀረቡ በመሆናቸው ያለ ንኪኪ ማስተር ካርድና ሌሎች ካርዶችን ይቀበላሉ፡፡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ንክኪ አልባ ማስተር ካርድ እና ቪዛ ይገልገሉ፡፡ የPOS እና የኤቲኤም አገልግሎቶችን ለመክፈልም ይጠቀሙ። በአሁኑ ወቅት ከ300 በላይ ኤቲኤም እና 1000+POSs በመላ አዲስ አበባ እና በተመረጡ የክልል ከተሞች ይገኛሉ።