ዘመን ባንክና የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ፋይናንስ ለማጠናከር የሚረዳ ስምምነት ተፈራረሙ

የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ዘመን ባንክን አዲሱ የአለም አቀፍ ንግድ ፋይናንስ ፕሮግራም Global Trade Finance Program (GTFP) አባል አድርጎ በመቀበል ባንኩ የኢትዮጵያን የወጪና ገቢ ንግድ ለማገዝ በሚያደርገው ጥረት የፋይናንስ ዋስትና እንደሚያቀርብ የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡ በዚህ ስምምነት የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የዘመን ባንክን የትሬድ ፋይናንስ (የወጪና ገቢ ንግድ ገንዘብ አቅርቦት) እንቅስቃሴ ለማጠናከርና በኢትዮጵያ […]

የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ዘመን ባንክን አዲሱ የአለም አቀፍ ንግድ ፋይናንስ ፕሮግራም Global Trade Finance Program (GTFP) አባል አድርጎ በመቀበል ባንኩ የኢትዮጵያን የወጪና ገቢ ንግድ ለማገዝ በሚያደርገው ጥረት የፋይናንስ ዋስትና እንደሚያቀርብ የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡

በዚህ ስምምነት የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የዘመን ባንክን የትሬድ ፋይናንስ (የወጪና ገቢ ንግድ ገንዘብ አቅርቦት) እንቅስቃሴ ለማጠናከርና በኢትዮጵያ ላሉ የወጪ ንግድ ላይ ለሚሰሩ ድርጅቶች አዲስ የንግድ ትስስርን ለመፍጠር የ30 ሚሊዮን ዶላር የትሬድ ፋይናንስ አቅርቦት ዋስትና ያቀርባል፡፡ 

ይህ ፕሮግራም ለባንኩ የትሬድ ፋይናንስ ድጋፍ በማቅረብ የኢትዮጵያን የወጪና ገቢ ንግድ ለመደገፍ ብሎም አህጉራዊ ንግድን ማበረታታትን አላማው ያደረገ ነው።

ዘመን ባንክ ከምስረታው ጀምሮ የሃገር ውስጥ እና የወጪ ንግድ ዘርፉ እንዲያድግና እንዲጎለብት የፋይናንስ አገልግሎትን በማቅረብና በማመቻቸት ሲሰራ የቆየ ሲሆን የንግድ ድርጅቶች ከተለያዩ ሃገራት ጋር የንግድ ትስስር እንዲፈጥሩ የበኩሉን አስተዋፅዎ እያበረከተ ይገኛል። ይህም የባንኩን ተቀባይነትና ተዓማኒነት በዓለም አቀፍ አጋሮቹ ዘንድ የበለጠ እንዲጨምር አድርጓል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ እነዚህ አገልግሎቶችና ፕሮግራሞች ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ አለመረጋጋት በሚኖርበት ወቅት በገቢና ወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩ የንግድ አጋሮችንም ሆነ የባንኩን ስጋት በእጅጉ እንደሚቀንስ የዘመን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ደረጀ ዘበነ ገልፀዋል፡፡

የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የትሬድ ፋይናንስ የአፍሪካን ቀጠናዊ የንግድ ልማት የሚያግዝና አህጉሪቱ ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኛነት ለመቀነስ አላማ ያደረገ የአንድ ቢሊዮን ዶላር የአፍሪካ ትሬድና አቅርቦት ሰንሰለት የፋይናንስ ፕሮግራም (Africa Trade and Supply Chain Finance Program (ATRI)) አካል ነው፡፡

የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የንግድ ፋይናንስ ዘርፉን የብድር አገልግሎት እና የቅድመ አደጋ አስተዳደር (Risk Management) እንዲሁም መካከለኛና አነስተኛ የሆኑ የንግድ ዘርፎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ የብድር አይነቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ የማማከር ስራንም ይሠራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የትሬድ ፋይናንስ አቅርቦት በአፍሪካ የንግድ ዘርፍ መጎልበት የሚያበረክተውአስተዋፅዎ ትልቅ መሆኑንና ዘመን ባንክ ከአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን Global Trade Finance Program (GTFP) ጋር የገባው ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ ወሳኝ ለሆኑት የሸቀጦች ንግድ ፋይናንስ ለማጠናከር እና ለሃገሪቱ አዲስ የንግድ አጋርነት በር ከፋች መሆኑን በኢትዮጵያ የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ስራ አስኪያጅ የሆኑት ማዳሎ ሚኖፉ ገልፀዋል፡፡ 

ይህ ፕሮግራም የወጪ ንግድ ፋይናንስ እንዳይስፋፋ የሚገድቡ እክሎችን ወይም ለዘርፉ ፈታኝ የሆኑ ስጋቶችን ለመቀነስ የሚረዳ ሲሆን ለወጪና ገቢ ንግድ ዘርፍ ፋይናንስ የማቅረብ አቅምንም ያሰፋል። በዚህ ፕሮግራም በኩል ዓለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን በአግሪ ቢዝነስ፣ በአምራች ዘርፍ፣ የግል ንግድ ዘርፍና ዲጂታል ዘርፍ ትኩረት በማድረግ በተለያዩ ዘርፎች ለተሰማሩ የፋይናንስ ተቋማት ከ100 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋስትና ሰጥቷል። ከዚህ ጋር በተያያዘም በ2023 እ.ኤ.አ ብቻ 9.1 ቢሊዮን ዶላር ዋስትና የሰጠ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 3.5 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነው ለአፍሪካ የተሰጠ ነው።

ስለ ዘመን ባንክ

ዘመን ባንክ የሚያስመዘግባቸው ውጤቶች የሚመነጩት ከፍተኛ ጥራት ያለው ልዩ የደንበኞች አገልግሎት ጋር ተደምሮ ለተለያዩ ቢዝነስ ተቋማት ማለትም ከግዙፍና ስመ-ጥር ድርጅቶች እስከ ግለሰብ ድረስ ላሉ የሚሆኑ በአማራጭ የተሞላ የባንክ አገልግሎቶቹ ነው፡፡ ተደራሽነቱንም በማስፋት በዋና መስሪያ ቤትና በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ከ117 በላይ ቅርንጫፍ ቢሮዎች በተቀላጠፈ ሁኔታ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

ዘመን ባንክ በመላው ሃገሪቱ ከሚገኙት ቅርንጫፎች በተጨማሪ እንደ ኤቲኤም፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ሞባይል ባንኪንግ፣ ደንበኞች ባሉበት ሄዶ አገልግሎት ማቅረብ፣ ፖስ እና ሌሎች የመሳሰሉ በርካታ የአገልግሎት አይነቶችን ለደንበኞች ያቀርባል። ይህ የቢዝነስ ሞዴል ትላልቅ ኮርፖሬሽኖች፣ የውጭ ባለሀብቶች፣ አነስተኛና የችርቻሮ ንግድ ያላቸው ደንበኞችን ጨምሮ ለተለያዩ ደንበኞች ምቹ የባንክ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ያስችላል።

ዘመን ባንክ በ2023 ዓ.ም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር የባንኩን ብራንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ስምምነት ፈፅሞ ወደ ስራ ገብቷል። በተጨማሪም ከፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ጋር በአጋርነት እየሰራ ይገኛል።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት: www.zemenbank.com ይጎብኙ።

ስለ አይ ኤፍ ሲ

የዓለም ባንክ ግሩፕ አባል (World Bank Group) የሆነው የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን በማደግ ላይ ያለውን የግል ዘርፍ ላይ የተለየ ትኩረት በማድረግ የሚደግፍ የልማት ተቋም ነው፡፡ አይ ኤፍ ሲ ከ100 በሚበልጡ ሃገሮች ውስጥ እየሰራ ሲሆን በታዳጊ አገሮች ውስጥ ገበያና የንግድ እድሎችን ለመፍጠር የካፒታል፣ የክህሎትና አቅምን በማሳደግ ረገድ ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።

በ2023 የበጀት ዓመት፣ አይ ኤፍ ሲ በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ለሚካሄዱ የግል ኩባንያዎችና የገንዘብ ተቋማት 43.7 ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር አበርክቷል፡፡ ይህም የገንዘብ ፈሰስ አላማው በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ውስጥ የግሉ ሴክተሩን አቅም በመጠቀም ሃገራቱን ከከፋ ድህነት ለማስወጣትና ሃገራት በኢኮኖሚ ረገድ በዓለም አቀፍ ቀውሶች ተጽእኖ ውስጥ በሚታገሉበት ጊዜ የጋራ ብልጽግናን ለማሳደግ የበኩሉን አስተዋፅዎ ያደርጋል። 

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት www.ifc.org ይጎብኙ።

ዘመን ባንክ አ.ማ

ግሩም ታሪኩ

ዳይሬክተር ማርኬቲንግና ኮሚዩኒኬሽንስ

+251-116 68 68 76

Girum.Tariku@zemenbank.com

Share