ዘመን ባንክ የኢትዮጲያ ኔዘርላንድስ ቢዝነስ ማህበር (ENLBA) አባል በመሆን አብሮ ለመስራት የሚያስችላለውን ስምምነት ነሐሴ 22 ቀን 2024 ዓ.ም. በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱ ዘመን ባንክ የኢትዮጵያ – ኔዘርላንድ ቢዝነስ ማህበር (ENLBA) ስር ካሉ ዘርፈ ብዙ ኢንዱስትሪዎች ጋር የሚኖረውን አጋርነትን ከማጠናከሩም በላይ ባንኩ ዘላቂ የባንክ እገዛ እና አጋርነትን ከሚፈልጉ መሰል ተቋማት ጋር አብሮ የመስራት እቅዱን ለማሳካት ያሰችለዋል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ማህበሩ እና አባላቱ የዘመን ባንክን ዘመናዊ እና ፈጠራ የታከለበት የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ።
የኢትዮጵያ- ኔዘርላንድ ቢዝነስ ማህበር (ENLBA) ለአባላቶቹ አስፈላጊ የሆኑ የሀብት ማሰባሰብ፤ ማማከር እና መሰል ድጋፎችን በማድረግ አባላቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖራቸውን የአጋርነት ሚና ከፍ በማድረግ የንግድ እና አንቨስትመንት አቅምን ለማሳለጥ የተቋቋመ ነው።
«ዘመን ባንክ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር ዘላቂና ጠንካራ አጋርነት በመገንባት ይታወቃል ። ባንኩ የደች (ኔዘርላንድስ) አበባና ፍራፍሬ ግብርና ማኑፋክቸሪንግ ኩባንያዎች ጋር አብሮ ሲሰራ ቆይቷል። አሁን የተደረሰበት አዲስ ትብብር ስምምነትም እነዚህን እና መሰል አጋርነትን ይበልጥ ከማጠናከሩም በላይ ለወደፊቱ ስልታዊ ጥምረትን በመፍጠር ዘላቂ አጋርነት እንዲመሰርት ያስችለዋል፡፡” ያሉት የዘመን ባንክ ተወካይ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስራት ታደሰ ናቸው።
«የኢትዮጵያ-ኔዘርላንድ የቢዝነስ ማህበር (ENLBA) የተቋቋመው በኢትዮጵያ የሚገኙ የደች (ኔዘርላንድ) ንግድ ድርጅቶችን በተሻለ ሁኔታ ለመደገፍና ለአዳዲስ የኔዘርላንድ ኢንቨስተሮች የመግቢያ በር ሆኖ ለማገልገል ነው። ከኢትዮጵያ ስኬታማ ባንኮች መካከል ከሆነው ዘመን ባነክ ጋር አብሮ በመስራት አባሎቻችን ለሚሰማሩበት የስራ መስኮች መንገድ ከመጥረግ አንፃር ሁኔታዎችን እጅግ ያቀልልናል ያሉት ሚስተር ሃዮ ሀምሰተር የENLBA ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ማህበራቸው በኢትዮጵያ ዕድገትና ስኬትን ላማሳለጥ ቁርጠኛ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።