ቅድመ-ገፅ » የንግድ አገልግሎቶች
ይህንን ሂሳብ ለመክፈት የሚያስፈልገው መነሻ ተቀማጭ ገንዘብ ብር 5,000 ሲሆን በወር ሊኖር የሚገባው አማካይ ወርሃዊ ዝቅተኛ ሂሳብ ብር 25,000 ነው። ይህንን ሂሳብ ሲጠቀሙ ደንበኞችም፤ ገደብ አልባ የቼክ መጠን የመፃፍ ፤ ኢንተርኔት ፣ ኤቲኤም ፣ ሞባይል ባንኪንግ እና የመሳሰሉት ሁሉን አቀፍ የባንክ አገልግሎቶች መጠቀም ይችላል ።
ዘመን ባንክ ልዩ የንግድ ቁጠባ እና ጥቅማጥቅሞችን ያቀርባል ይህም የቁጠባ እና የቼክ ሂሳብ ባህሪያትን አጣምሮ የያዘ ሲሆን ጠቀም ያለ ወለድም ያስገኛል፡፡ በተጨማሪም በተሰጡት ቼኮች ላይ ክፍያ ማረጋገጥ ያሰችላል ። ይህንን ሂሳብ ለመጠቀም ወር እሰከ ወር ቢያንስ ብር 100,000 በሂሳቡ መገኘት አለበት፡፡ ሂሳቡን በማንኛውም መጠን ከከፈቱ በኋላ ቀሪ ሂሳቡን ለማሳደግ የአስር ቀናት የምህረት ጊዜ አለ ። ይህንን ሂሳብ ለመጠቀም የሚያስፈልገው የቅዲሚያ ተቀማጭ ገንዘብ ብር 5,000 ነው።
የቼክ እና የቁጠባ ሂሳብ ያለው አንድ ደንበኛ የቼክ ሂሳቡን እንደ ኦቨር ድራፍት መጠባባቂያ የመጠቀም አማራጭ አለው። ደንበኛው በቼክ ሂሳቡ ላይ ቼክ ቢጽፍ እና በቂ ገንዘብ ከሌለው ከዚያ ከቁጠባ ሂሳቡ የሚገኘው ገንዘብ ልዩነቱን ለመሸፈኛ ሊገለገል ይችላል ለዚህም 20 ብር ብቻ ይከፈላል።
ዘመን ባንክ እንደ የብድር ፍላጎቶችዎ ለእርስዎ የተለያዩ አማራጮች ይዞሎት ቀርቧል ።
የቢዝነስ ባለቤቶች የተለያዩ የብድር ፍላጎቶች አሏቸው። ለአንዳንዶች ብድር የአጭር ጊዜ የገንዘብ ፍሰት ማሟያ ሲሆን ለሌሎች ደግሞ ለአዳዲስ መሳሪያዎች የመግዣ ፋይናንስ ነው። ከዚህም በላይ ሁሉም የብድር ውሳኔዎቻችን የሚወሰኑት ስለ ንግድዎ ልዩነት በሚገባ በሚያውቁ የአካባቢው የንግድ ወኪሎቻችን ነው። በዘመን ባንክ ፈጣን መልስና ግላዊ አገልግሎት ያገኛሉ።
Feb 14, 2025
Currency ConverterEUR
GBP
CAD
AED
SAR
CNY
CHF
SEK
JPY
KES
ZAR
USD