ቅድመ-ገፅ » የካርድ ግላዊነት ማላበስ አገልግሎት
ዘመን ባንክ በኢንዱስትሪ ውስጥ ካሉ ጥቂት ባንኮች አንዱ በመሆን የካርድ ግላዊነት ማላበሻ አገልግሎቶችን በ PCI DSS መስፈርቶች መሰረት በቋሚነት ለዚህ ተብሎ በተቋቋመ ጽ/ቤት አገልግሎት እየሰጠ ነው። በኢትዮጵያ የፒሲአይ ዲኤስኤስ በተሟላ ሁኔታ በመጠቀም የመጀመሪያ ባንክ በመሆኑ ዘመን ባንክ ይህንን አቋም ጠብቆ በየአመቱ የሚታደስ የምስክር ወረቀት አግኝቷል።
የባንኩ የካርድ ግላዊነትን የማላበስ ውስጣዊ አገልግሎት የፕላቲኒየም ቅድመ ክፍያ የጉዞ ማስተር ካርድን ጨምሮ የተለያዩ ምርቶችን ያቀርባል፡፡ ይህም ዘመን ባንክን ዓለም አቀፍ የጉዞ ካርድን ለማስተዋወቅ በኢትዮጵያ ቀዳሚ ባንክ ያደርገዋል። ከዚህም በላይ ዘመን ባንክ ለደንበኞቹ የተለያዩ የደንበኞችን ፍላጎት በማሟላት የዴቢት ካርዶችን ፣ የቅድመ ክፍያ የሀገር ውስጥ ካርዶችን እና የስጦታ ካርዶችን ያቀርባል፡፡
የዘመን ዴቢት ካርዶች 24 ሰዓት ሙሉ በሂሳብዎ እንዲገለገሉ ያደርጋል። የኛ ንክኪ የሌለው ዴቢት ካርድ ከኤቲኤም ካርድ በላይ ነው፤ ይህም በ POS ተርሚናል ፣ በኦንላይን ግብይት እና በኤቲኤም ላይ ያለ ጥሬ ገንዘብ ግብይቶችን እንዲያደርጉ ያስችልዎታል። መሰረታዊ ፣ የግል ፣ ፕሪስቲጅ እና የዜድ ክለብ ዴቢት ካርዶችን እናቀርባለን።
ዘመናዊ የንግድ ድርጅቶችን ፍላጎት ለማሟላት የተዘጋጀው የደመወዝ ካርዳችን የሠራተኞችን ደመወዝ በደመወዝ ካርዳቸው በኩል በማሰራጨት አስተማማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት ይሰጣል ። እንደ አመቺነቱና ተደራሽነቱ የክፍያ አማራጭ በመስጠት የደመዝ ክፍያ ሂደቱን ማመቻቸት ይችላሉ ።
በዘመን ባንክ የቅድመ ክፍያ ካርድ አማካኝነት በየቀኑ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያወጡ ሙሉ ቁጥጥር ማድረግ ይችላሉ። በቅድመ ክፍያ ካርድ ላይ ያለው የገንዘብ መጠን ሊከፈል የሚችል ከፍተኛው መጠን ነው። የቅድመ ክፍያ ካርዱን ለሁሉም የክፍያ ፍላጎቶችዎ በካርዱ ለመጠቀም በበይነመረብ እና በሞባይል ባንኪንግ አማካይነት ለጉዞና ለግብይት የሚያስፈልግዎትን ገንዘብ መሙላት ይችላሉ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የቅድመ ክፍያ ካርድ በመጠቀም በካርዱ ላይ የተጻፈውን ገንዘብ ብቻ ማውጣት ስለሚቻል ከአጭበርባሪዎች ራስን ለመጠበቅና ከመጠን በላይ ገንዘብ ከማውጣት መከላከል ይቻላል። ከዚህም በተጨማሪ ወጪንና በጀትን በተገቢው መንገድ ለመቆጣጠር ያስችላል።
ለዓመት በዓል፣ ለልደት፣ ለክብረ በዓልና ለመሳሰሉት ዝግጅቶች ጥሩ ስጦታ መስጠት ይፈልጋሉ? የትኛውንም የባንካችንን ቅርንጫፎች ወይም ወኪሎቻችንን በማነጋገር ይህንን አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡ የዘመን ስጦታ በኮርፖሬት ደረጃ ለሠራተኞች፣ ለበዓላትና ለአጋሮች ወዘተ ስጦታ ለመስጠት ሊውል ይችላል፡፡
የስጦታ ካርዶቻችን በሁሉም የዘመንና የሌሎች ባንኮች ፖስ እና ኤቲኤም ማሽኖች ተቀባይነት ስላላቸው ፣ ገንዘብ ወጪ ለማድረግና ለመክፈል ያስችላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በስጦታ ካርድ ላይ የተቀመጠውን ገንዘብ ለማውጣትም ያመቻል፡፡
የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የቅድመ ክፍያና ንክኪ አልባ የጉዞ ካርድ ኢትዮጵያውያን ተጓዦች ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር የዩኤስ ዶላር ወይም ዩሮ ምንዛሬዎች እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል ።
ይህ ምርት ደንበኞቻችን በውጭ ሀገራት ለሚያደርጓቸው ጉዞዎች ያለ ጥሬ ገንዘብ እንዲገለገሉ ያደርጋቸዋል፡፡ የዘመን ባንክ በሀገሪቱ ውስጥ የባንክ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ የሚታወቅ ሲሆን ለደንበኞቻችን ደህንነትና ምቾት በማስተር ካርድ አጋርነት የንክኪ አልባ የቅድመ ክፍያ የጉዞ ካርዶችን ቀዳሚ ሆኖ በማቅረቡ ኩራት ይሰማዋል ።
ያለካርድ ገንዘብ ማውጣት አገልግሎታችን አማካኝነት ካርድ ሳይዙ በዘመን ባንክ ኤቲኤም ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ ። ካርድ አልባው መፍትሄ ካርድዎን በኪስዎ አስቀምጠውና በሞባይል ስልክዎ ገንዘብ እንዲያወጡ ያስችልዎታል።
የዲጂታል ባንኪንግ አቅርቦታችን በሞባይልና በበይነመረብ ባንኪንግ የላቀ አገልግሎት የምንሰጥበት ነው፡፡ ደንበኞች በቀላሉ እንዲጠቀሙና ራሳቸውን ችለው የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
Feb 14, 2025
Currency ConverterEUR
GBP
CAD
AED
SAR
CNY
CHF
SEK
JPY
KES
ZAR
USD