ቅድመ-ገፅ » የኮንሲዩመር ቁጠባ
የዘመን ባንክ የቁጠባ ሂሳቦች በግል እና በቢዝነስ የተከፋፈሉ ሲሆኑ በውስጣቸው የቁጠባ፣ የቼክ እና የረጅም ጊዜ የቁጠባ ሂሳቦችን የያዙ ናቸው፡፡
አብዛኞቹ የቁጠባ ሂሳቦች ለደንበኞች ገንዘባቸውን በቁጠባ ሂሳብ ውስጥ በማስቀመጥ ክፍያዎችን በቼክ ማንቀሳቀስ ያስችላቸዋል፣ ይህም ያለ ተጨማሪ ተቀማጭ ገንዘብ መክፈት ይችላሉ፡፡
የኮንሲዩመር ቁጠባ ሂሳቦች የቁጠባና የቼኪንግ በግለሰቦች የሚከፈትና የሚንቀሳቀስ በአብዛኛው ለንግድ ነክ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎች የሚከፈት የቁጠባ ሂሳብ ነው፡፡
የኮንሲዩመር ቁጠባ ሂሳብ ሁሉም የዘመን ባንክ ደንበኞች መጠቀም የሚችሉት የቁጠባ ሂሳብ አይነት ነው፡፡ አካውንቱን ሲከፍቱ ሁሉም ደንበኞች የዴቢት ካርድ ያገኛሉ በተጨማሪም የባንኩን የቴክኖሎጂ አማራጮች ኦምኒ–ቻናል ባንክ አገልግሎት ኤቲኤም፣ የኢንተርኔት ባንክ አገልግሎት፣ የጥሪ ማእከል ባንክ እና የኤስኤምኤስ ባንኪንግን ወዲያውኑ ያገኛሉ።
የዘመን ባንክ ፐርሰናል ባንኪንግ ለደንበኞች ከ5000 ብር ጀምሮ አካውንቱን መክፈት ያስችላቸዎል፡፡ ይህን አካውንት የሚከፍቱ ደንበኞች ከመሰረታዊ የባንክ አገልግሎት በተጨማሪ የሞባይልና ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ የኤቲኤም እና የኤስኤምኤስ አገልግሎትን ጨምሮ መሰረታዊ የባንክ አገልግሎት ያገኛሉ። የፐርሰናል ቁጠባ ሂሳብ ያላቸው ደንበኞች በየእለቱ ዝቅተኛ ቀሪ ሒሳባቸው እና በተቀናጀ ወርሃዊ ተቀማጭ ቢያንስ 7% ወለድ ያገኛሉ።
ይህንን ሂሳብ ወርሃዊ 100,000 ብር የሚያስቀምጡ ደንበኞች መክፈት ይችላሉ፡፡ ይህንን አካውንት የሚከፍቱ ደንበኞች የቀን ሒሳባቸው ተሰልቶ የተሻለ የወለድ መጠን 7.25% ያገኛሉ፡፡ የደንበኞች ፋይናንስ እንቅስቃሴዎች ታይቶ ባንኩ ለደንበኞቹ በፋይናንስ በእንቅስቃሴዎቻቸው እንዲያግዛቸው በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፐርሰናል ባንከር ይመድብላቸዎል፡፡
የዚ–ክለብ ቁጠባ ሂሳብ ደንበኞች ልዩ መታወቂያቸውን በመጠቀም በሁሉም የዘመን ባንክ ቅርንጫፎች አገልግሎት ለማግኘት ቅድሚያ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪ በልዩ ሁኔታ የተዘጋጁ ከዕለታዊ የብር ወጪ ገደብ በላይ ማውጣት የሚያስችሉ የኤቲኤም ካርዶች ያገኛሉ፡፡
የሂሳቡ ባለቤቶች አብዛኛዎቹን የባንኩን አገልግሎቶች በነፃ ያገኛሉ። በተጨማሪም እንደ ፍላጎታቸው እና የመበደር አቅማቸው ኮንሲዩመር ብድር ይመቻችላቸዋል፡፡
የዚ ክለብ ቁጠባ ሂሳብ ደንበኞች ተቀማጭ ገንዘባቸውን ከፍ ወዳለ ምድብ እና ይበልጥ ማራኪ የወለድ መጠን እንዲያሳድጉ ለማበረታታት የዚ ክለብ ቤዚክ፣ጎልድ እና ፕላቲኒየም ምድቦች ተከፍሏል። ደንበኞች ብዙ ሲቆጥቡ ማራኪ በሆነው በቀን በዝቅተኛው ሂሳብ በወርሃዊ ስሌት በሚሰራው ስሌት ወለድ በማግኘት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
ደንበኞች የዚ ክለብ ቤዚክ ሂሳብ ከብር 500,000.00 በላይ፣ የዚ ክለብ ጎልድ በ2,000,000 እና ፕላቲኒየም
በ5,000,000 ብር መክፈት ይችላሉ። ሆኖም እያንዳንዱን ሂሳብ በብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) መከፈት ይችላሉ።
ይህ የቁጠባ ሂሳብ ለተለያዩ የግል፣ የመንግስት እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅት ስራ አስፈፃሚዎች ወይም ከፍተኛ አስተዳዳሪዎች ታስቦ የተዘጋጀ የቁጠባ ሂሳብ ነው።
የልዩ የስራ አስፈፃሚዎች የቁጠባ ሂሳብ ደንበኞች የተለየ በቅርንጫፎች ለአገልግሎት ቅድሚያ የሚያሰጣቸው ልዩ የደንበኛ መለያ ቁጥር ይሰጣቸዋል፡፡ በተጨማሪም በኤቲኤም እንደየሂሳቡ አይነት እስከ ብር 20,000.00 የሚደርስ ከፍተኛ በየቀኑ ገንዘብ ማውጣት የሚያስችል ልዩ የኤቲኤም ካርድ ያገኛሉ፡፡
የልዩ የስራ አስፈፃሚዎች የቁጠባ ሂሳብ በቼክ የሚሰሩ የቁጠባ እና የከረንት ሂሳቦችን ያጣመረ ሂሳብ ነው። ይህ የቁጠባ ሂሳብ በቀን በዝቅተኛው ሂሳብ በወርሃዊ ስሌት የሚሰራ ማራኪ ወለድ ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡
ደንበኞች ቁጠባቸው ከፍ እያለ በሄደ ቁጥር በቤዚክ፣ ወርቅ እና ፕላቲነም ሂሳብ አይነቶች መሰረት የሚሰላ ማራኪ ወለድ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
ደንበኞች የልዩ የስራ አስፈፃሚዎች ቤዚክ ሂሳብ ከብር 100,000.00 በላይ፣ የልዩ ቁጠባ ሂሳብ ብር 300,000.00 ፣ የጎልድ በ500,000.00 እና ፕላቲኒየም በ1,000,000 መክፈት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ደንበኞች ሁሉንም አካውንቶች በብር 10,000.00 መነሻ ሂሳብ መክፈት ይችላሉ፡፡
በተጨማሪም ሌሎች የድርጅቱ ሰራተኞች 50% የደመወዝ ቅድመ ክፍያ ማግኘት ይችላሉ። ሁሉም ሰራተኞች የኮንሲዩመር ብድር ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
የዚ ክለብ የልጆች ቁጠባ ሂሳብ መደበኛ የቁጠባ ሂሳብ ከፍ ያለ በቀን በዝቅተኛው ሂሳብ በወርሃዊ ስሌት የሚሰራ ወለድ የሚያስገኝ የቁጠባ ሂሳብ አይነት ነው፡፡ ይህ ሂሳብ ቤዚክ ዚ ክለብ ህጻንት፣ ልዩ እና ኤክስክሉሲቭ የህጻንት የተከፈለ የሂሳቡን ባለቤቶች ቁጠባቸውን እንዲያሳድጉ እና የተሻለ ወለድ እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
ደንበኞች የዚ ክለብ የልጆች ቁጠባ ሂሳብ ቤዚክ ሂሳብ ከብር 1,000.00 ጀምሮ፣ የልዩ ቁጠባ ሂሳብ ከብር 50,000.00 እና ልዩ የህጻንት ከብር 1,000 ጀምሮ መክፈት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ደንበኞች ሁሉንም አካውንቶች በብር 1000.00 መነሻ ሂሳብ መክፈት ይችላሉ፡፡
የወጣቶች የቁጠባ ሂሳብ በቤዚክ፣ ልዩ እና ኤክስክሉሲቭ የወጣቶች ይከፈላል፡፡ ደንበኞች ቤዚክ ቁጠባ ሂሳብ ከብር 1,000.00 ጀምሮ፣ የልዩ ቁጠባ ሂሳብ ከብር 100,000.00 እና ልዩ የወጣቶች ከብር 200,000.00 ጀምሮ መክፈት ይችላሉ፡፡ነገር ግን ልዩ እና ኤክስክሉሲቭ የወጣቶች ቁጠባ ሂሳብ በብር 1000.00 መነሻ ሂሳብ መክፈት ይችላሉ፡፡
በየቀኑ የሚሰላ ወለድ በተጨማሪም በቴክኖሎጂ የተደገፉ የደንበኞች ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ አገልግሎቶችን ያቀርባል፡፡
Feb 14, 2025
Currency ConverterEUR
GBP
CAD
AED
SAR
CNY
CHF
SEK
JPY
KES
ZAR
USD