ዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት

የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት

ለማንኛውም የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ዘመን ባንክ  የእርስዎ ምርጫ ነው

ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ የተዘጋጀ የቁጠባ ሂሳብ

ይህ የቁጠባ ሂሳብ ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ ሂሳቡን ለመክፈት መስፈርቶቹን ለሚያሟሉ (በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ምንዛሪ) ለሚከፈላቸው በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እና በዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች በውጭ ንግድ ማህበረሰብ ግለሰቦች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ሰራተኞቻቸው የተዘጋጀ ነው፡፡ ይህ ወለድ የሌለው የቼኪንግ ቁጠባ ሂሳብ፡፡  በዘመን ባንክ ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ ከተዘጋጁት የቁጠባ ሂሳቦች ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው።

ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ሂሳቦች (NR-FCY A/C)

በዚህ የቁጠባ ሂሳብ ውስጥ ያለው ቀሪ ሒሳብ በውጭ ምንዛሪ ይቀመጣል። የዚህ ሂሳብ ተቀማጭ በጥሬ ገንዘብ ምንዛሪ በመላክ፣ በውጭ አገር ገንዘብ እና ከኢትዮጵያዊ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ሂሳቦች ቼክ መሆን ይችላል፡፡ የዚህ ሂሳብ ባለቤቶች ለውጭ ሀገር ጉዞዎቻቸው፣ለውጭ ሀገር ተልእኮአቸው እና ለውጪ ሀገራት ክፍያዎቻቸው  ከሂሳባቸው በውጪ ምንዛሪ ማውጣት ይችላሉ፡፡ በኢትዮጵያ ብርም ክፍያ መፈፀም ይችላሉ፡፡

ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ የማይተላለፍ ብር ሂሳብ (NR-T BIRR A/C)

ይህ ሂሳብ ከኢትዮጵያዊ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ሂሳቦች (NR-FCY A/C) ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነገርግን በብር የሚቀመጥ ነው፡፡ ከዚህ ሂሳብ አስፈላጊውን ማስረጃ ሰነዶች በመያዝ በውጪ ምንዛሪ ለውጪ አገራት ጉዞ ውይም ለሌሎች ክፍያዎች ማድረግ ይቻላል፡፡

ነዋሪ ያልሆኑ የማይተላለፉ ብር ሒሳቦች (NR-NT BIRR A/C)

ይህ ሂሳብ በአገር ውስጥ በብር ክፍያዎችን ለመፈጸም እና በውጭ አገር ለሚኖሩ ተጠቃሚዎች ክፍያ ለመፈጸም የውጭ ምንዛሪ ፈቃድ ማግኘት ያስፈልጋቸዋል፡፡

ትርፍ ወደ ሀገር ቤት መመለስ

ዘመን ባንክ ለውጭ አገራት ኩባንያዎች ትርፋቸውን ወደ ሀገራቸው በታቀደ መልኩ እና በላቀ የደንበኞች አገልግሎት ለመመለስ የተዘጋጀ አገልግሎት ነው፡፡

ዘመን ባንክ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ለታላላቅ የውጭ ኩባንያዎች የዲቪደንድ ተመላሽ ሂደቶችን በማከናወን ረገድ ብዙ ልምድ አለው። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ደንብ መሠረት ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ከታወቁ የውጭ ኢንቨስትመንቶች ትርፍ ወይም የትርፍ ድርሻ የሚያገኙ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ወይም አስፈላጊዎቹ ሰነዶች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሲፀድቁ እና ሲሟሉ ከትርፉ ተመጣጣኝ የሆነ ድርሻ ወይም ካፒታል  ላይ ተመጣጣኝ ተመላሽ የማግኘት መብት አላቸው፡፡