ቅድመ-ገፅ » የዘመን ባንክ የቁጠባ ሂሳቦች
የዘመን ባንክ የቁጠባ ሂሳቦች በግል እና በቢዝነስ የተከፋፈሉ ሲሆኑ በውስጣቸው የቁጠባ፣ የቼክ እና የረጅም ጊዜ የቁጠባ ሂሳቦችን የያዙ ናቸው፡፡
አብዛኞቹ የቁጠባ ሂሳቦች ለደንበኞች ገንዘባቸውን በቁጠባ ሂሳብ ውስጥ በማስቀመጥ ክፍያዎችን በቼክ ማንቀሳቀስ ያስችላቸዋል፣ ይህም ያለ ተጨማሪ ተቀማጭ ገንዘብ መክፈት ይችላሉ፡፡
የኮንሲዩመር ቁጠባ ሂሳቦች የቁጠባና የቼኪንግ በግለሰቦች የሚከፈትና የሚንቀሳቀስ በአብዛኛው ለንግድ ነክ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎች የሚከፈት የቁጠባ ሂሳብ ነው፡፡
የኮንሲዩመር ቁጠባ ሂሳብ ሁሉም የዘመን ባንክ ደንበኞች መጠቀም የሚችሉት የቁጠባ ሂሳብ አይነት ነው፡፡ አካውንቱን ሲከፍቱ ሁሉም ደንበኞች የዴቢት ካርድ ያገኛሉ በተጨማሪም የባንኩን የቴክኖሎጂ አማራጮች ኦምኒ–ቻናል ባንክ አገልግሎት ኤቲኤም፣ የኢንተርኔት ባንክ አገልግሎት፣ የጥሪ ማእከል ባንክ እና የኤስኤምኤስ ባንኪንግን ወዲያውኑ ያገኛሉ።
የዘመን ባንክ ፐርሰናል ባንኪንግ ለደንበኞች ከ5000 ብር ጀምሮ አካውንቱን መክፈት ያስችላቸዎል፡፡ የፐርሰናል ቁጠባ ሂሳብ ያላቸው ደንበኞች በየእለቱ ዝቅተኛ ቀሪ ሒሳባቸው እና በተቀናጀ ወርሃዊ ተቀማጭ ቢያንስ 7% ወለድ ያገኛሉ።
የዘመን ባንክ ፐርሰናል ባንኪንግ ለደንበኞች ከ5000 ብር ጀምሮ አካውንቱን መክፈት ያስችላቸዎል፡፡ የፐርሰናል ቁጠባ ሂሳብ ያላቸው ደንበኞች በየእለቱ ዝቅተኛ ቀሪ ሒሳባቸው እና በተቀናጀ ወርሃዊ ተቀማጭ ቢያንስ 7% ወለድ ያገኛሉ።
ይህንን ሂሳብ ወርሃዊ 100,000 ብር የሚያስቀምጡ ደንበኞች ከ5000 ብር ጀምሮ አካውንቱን መክፈት ይችላሉ፡፡ ይህንን አካውንት የሚከፍቱ ደንበኞች የቀን ሒሳባቸው ተሰልቶ የተሻለ የወለድ መጠን 7.25% ያገኛሉ፡፡
ይህንን ሂሳብ ወርሃዊ 500,000 ብር የሚያስቀምጡ ደንበኞች ከ5000 ብር ጀምሮ አካውንቱን መክፈት ይችላሉ፡፡
የዚ–ክለብ ቁጠባ ሂሳብ ደንበኞች ልዩ መታወቂያቸውን በመጠቀም በሁሉም የዘመን ባንክ ቅርንጫፎች አገልግሎት ለማግኘት ቅድሚያ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪ በልዩ ሁኔታ የተዘጋጁ ከዕለታዊ የብር ወጪ ገደብ በላይ ማውጣት የሚያስችሉ የኤቲኤም ካርዶች ያገኛሉ፡
ወለድ የማይታሰብለት የሂሳብ አይነት ነው፡፡ ይህ የቁጠባ ሂሳብ እንደ ፓኬጅ የፐርሰናል ቁጠባ ሂሳብ ያለ ተጨማሪ ተቀማጭ ብር መስፈርቶች የፐርሰናል ቁጠባ ሂሳብ በቼክ ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ያስችላቸዋል፡፡
ወለድ የማይታሰብለት የሂሳብ አይነት ነው፡፡ ይህ የቁጠባ ሂሳብ እንደ ፓኬጅ ከፕሪስቲጅ ቁጠባ ሂሳብ ያለ ተጨማሪ ተቀማጭ ብር መስፈርቶች ሂሳቡን በቼክ ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ያስችላቸዋል፡፡
ይህን የቁጠባ ሂሳብ እንደ ፓኬጅ ደንበኞች ዚ-ክለብ ቼኪንግ ያለ ተጨማሪ መስፈርቶች መክፈት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ደንበኞች በተቀማጭ ገንዘብ ላይ የተሻለ ወለድ እያገኙ ሂሳቡን በቼክ ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ያደርጉታል፡፡
ደንበኞች ተቀማጭ ገንዘባቸውን ከፍ ወዳለ ምድብ እና ይበልጥ ማራኪ የወለድ መጠን እንዲያሳድጉ ለማበረታታት የዚ ክለብ ቤዚክ፣ጎልድ እና ፕላቲኒየም ምድቦች ተከፍሏል። ደንበኞች ብዙ ሲቆጥቡ ማራኪ በሆነው በቀን በዝቅተኛው ሂሳብ በወርሃዊ ስሌት በሚሰራው ስሌት ወለድ በማግኘት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
ደንበኞች የዚ ክለብ ቤዚክ ሂሳብ ከብር 500,000.00 በላይ፣ የዚ ክለብ ጎልድ በ2,000,000 እና ፕላቲኒየም በ5,000,000 ብር መክፈት ይችላሉ። ሆኖም እያንዳንዱን ሂሳብ በብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) መከፈት ይችላሉ።
ይህ የቁጠባ ሂሳብ ለተለያዩ የግል፣ የመንግስት እና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅት ስራ አስፈፃሚዎች ወይም ከፍተኛ አስተዳዳሪዎች ታስቦ የተዘጋጀ የቁጠባ ሂሳብ ነው።
የልዩ የስራ አስፈፃሚዎች የቁጠባ ሂሳብ ደንበኞች የተለየ በቅርንጫፎች ለአገልግሎት ቅድሚያ የሚያሰጣቸው ልዩ የደንበኛ መለያ ቁጥር ይሰጣቸዋል፡፡ በተጨማሪም በኤቲኤም እንደየሂሳቡ አይነት እስከ ብር 20,000.00 የሚደርስ ከፍተኛ በየቀኑ ገንዘብ ማውጣት የሚያስችል ልዩ የኤቲኤም ካርድ ያገኛሉ፡፡
የልዩ የስራ አስፈፃሚዎች የቁጠባ ሂሳብ በቼክ የሚሰሩ የቁጠባ እና የከረንት ሂሳቦችን ያጣመረ ሂሳብ ነው። ደንበኞች የልዩ የስራ አስፈፃሚዎች ቤዚክ ሂሳብ ከብር 100,000.00 በላይ፣ የልዩ ቁጠባ ሂሳብ ብር 300,000.00 ፣ የጎልድ በ500,000.00 እና ፕላቲኒየም በ1,000,000 መክፈት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ደንበኞች ሁሉንም አካውንቶች በብር 10,000.00 መነሻ ሂሳብ መክፈት ይችላሉ፡፡
በተጨማሪም ሌሎች የድርጅቱ ሰራተኞች 50% የደመወዝ ቅድመ ክፍያ ማግኘት ይችላሉ። ሁሉም ሰራተኞች የኮንሲዩመር ብድር ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
የዚ ክለብ የልጆች ቁጠባ ሂሳብ መደበኛ የቁጠባ ሂሳብ ከፍ ያለ በቀን በዝቅተኛው ሂሳብ በወርሃዊ ስሌት የሚሰራ ወለድ የሚያስገኝ የቁጠባ ሂሳብ አይነት ነው፡፡
ደንበኞች የዚ ክለብ የልጆች ቁጠባ ሂሳብ ቤዚክ ሂሳብ ከብር 1,000.00 ጀምሮ፣ የልዩ ቁጠባ ሂሳብ ከብር 50,000.00 እና ልዩ የህጻንት ከብር 1,000 ጀምሮ መክፈት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ደንበኞች ሁሉንም አካውንቶች በብር 1000.00 መነሻ ሂሳብ መክፈት ይችላሉ፡፡
የወጣቶች የቁጠባ ሂሳብ በቤዚክ፣ ልዩ እና ኤክስክሉሲቭ የወጣቶች ይከፈላል፡፡ ደንበኞች ቤዚክ ቁጠባ ሂሳብ ከብር 1,000.00 ጀምሮ፣ የልዩ ቁጠባ ሂሳብ ከብር 100,000.00 እና ልዩ የወጣቶች ከብር 200,000.00 ጀምሮ መክፈት ይችላሉ፡፡ነገር ግን ልዩ እና ኤክስክሉሲቭ የወጣቶች ቁጠባ ሂሳብ በብር 1000.00 መነሻ ሂሳብ መክፈት ይችላሉ፡፡
የረጅም ጊዜ ተቀማጭ ደንበኞች ለተወሰነ ጊዜ ገንዘባቸውን ለረጅም ጊዜ በዝግ ሂሳብ ማስቀመጥ የሚችሉበት አገልግሎት ነው፡፡ በረጅም ጊዜ ተቀማጭ ደንበኞች የተሻለ ወለድ እና ለገንዘባቸው ዋስትና ማግኘት ያችላሉ፡፡ ከብር 1,000,000 መነሻ ጀምሮ ዘመን ባንክ የተለያዩ የረጅም ጊዜ ተቀማጭ አማራጮችን ያቀርባል፡፡
ከሌሎች የቁጠባ ሂሳቦች የበለጠ ወለድ ያስገኛሉ።
ወለድ በቅድሚያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በዘመን ባንክ የሚያገኙትን ወለድ በረጅም ጊዜ ተቀማጭ ወይም በዘመን ቼኪንግ ቁጠባ ሒሳቦች ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡
የዘመን ባንክ የረጅም ጊዜ ተቀማጭ በቅናሽ ዋጋ ለዘመን ብድር ማስያዣ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።
የዲያስፖራ ቁጠባ ሒሳቦች ከአንድ ዓመት በላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ለሚሠሩና ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ የውጭ አገር ዜጎች እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተጨማሪም ከላይ በተገለጹት በባለቤትነት ለተያዙ የንግድ ተቋማት የተዘጋጁ ሂሳቦች ናቸው፡፡
የዲያስፖራ ቁጠባ ሒሳቦች መለያዎች
በዲያስፖራ ቁጠባ ሒሳቦች የሚቀመጡት በውጭ ምንዛሪ ነው። ይህን አካውንት በቼክ ወይም በኤሌክትሮኒክ የክፍያ ማንቀሳቀስ ይቻላል። ብቁ ደንበኞች ሂሳቦቹን በUSD፣ GBP ወይም ዩሮ ለመክፈት መምረጥ ይችላሉ። ሂሳቡን ለመክፈት 100 የአሜሪካን ዶላር/ፓውንድ/ ዩሮ ሲያስፈልግ፣ ተጨማሪ ገቢ ገንዘቦች በጉምሩክ ከተገለጸ፣ ከጉዞ ወጪ የሚመለስ ገንዘብ ከሆነ ወይም ነዋሪ ካልሆኑ የውጭ ምንዛሪ እና ከሌሎች በዲያስፖራ ቁጠባ ሒሳቦች የሚተላለፉ እና ከየውጭ አገር ዜጎች ሂሳብ የተወሰዱ ቼኮች ተጨማሪ ገንዘቦችን በውጭ ምንዛሪ ማስገባት ይችላሉ።
የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ኩባንያዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ኤምባሲዎች እና የውጭ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ይህን አካውንት ለመክፈት ብቁ ናቸው። ይህ አካውንት በ USD፣ EUR፣ GBP ወይም በብሄራዊ ባንክ ተቀባይነት ያለው የውጭ ምንዛሪ ሊከፈት ይችላል። የውጭ ኩባንያዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ኤምባሲዎች እና የውጭ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ይህንን ሂሳብ ተጠቅመው ያለ ምንም ገደብ ለውጭ ሀገር ክፍያዎች ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ዜግነት ላላቸው፣ የውጭ ሀገር ነዋሪ ጊዜያዊ ወይም ቋሚ የመኖሪያ ፍቃድ ያለው እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ይህንን አካውንት ለመክፈት ብቁ ናቸው። ይህ አካውንት በ USD፣ EUR፣ GBP ወይም ሌላ በብሄራዊ ባንክ ተቀባይነት ያለው የውጭ ምንዛሪ ሊከፈት ይችላል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ ላልሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ኢትዮጵያውያን ከአንድ አመት በላይ ለስራ ወይም ኑሮቸውን ውጭ አገር ላደረጉ፣ ኢትዮጵያውያን ከአንድ አመት በላይ ውጪ አገር ለመሄድ በሂደት ላይ ያሉ እና ማረጋገጫ ሰነዶችን ማቅረብ የሚችሉ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ነዋሪ ባልሆኑ ባለቤትነት የተያዙ የንግድ ድርጅቶች እና ከኢትዮጵያ ውጪ የሚገኙ የንግድ ድርጅቶች ይህንን ሂሳብ መክፈት ይችላሉ፡፡ይህ አካውንት በ USD፣ EUR፣ GBP ወይም ሌላ በብሄራዊ ባንክ ተቀባይነት ያለው የውጭ ምንዛሪ ሊከፈት ይችላል።
በብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ኖቶችን እና የክሬዲት ካርድ/ዴቢት ካርድ/ቅድመ ክፍያ ካርድ እና ክፍያ ለመፈጸም ፈቃድ የተሰጣቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላኪ፣ነጋዴዎች እና/ወይም ድርጅቶች ይህንን አካውንት የውጪ ምንዛሪያቸውን ይዘው ለመቆየት መክፈት ይችላሉ፡፡ ይህ አካውንት በ USD፣ EUR፣ GBP ወይም ሌላ በብሄራዊ ባንክ ተቀባይነት ባለው የውጭ ምንዛሬ ሊከፈት ይችላል።
Feb 14, 2025
Currency ConverterEUR
GBP
CAD
AED
SAR
CNY
CHF
SEK
JPY
KES
ZAR
USD