🔊 Reader Off

ዲጂታላይዜሽን እና አጋርነት

ዲጂታላይዜሽን እና አጋርነት

ዘመን ባንክ በዲጂታላይዜሽን  ጉልህ እድገት ማሳየቱን ቀጥሏል። ባንኩ ተደራሽነትን ለማሻሻል አውቶማቲክን ለመጨመር ደህንነትን ለማረጋገጥ እና ተወዳዳሪነቱን ለማጠናከር የታለሙ ፕሮጀክቶችን በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል እነዚህ ጥረቶች ለደንበኞች የሚመቹ መፍትሄዎችንና ማሻሻያዎችን ፈጥረዋል። የዘመን ባንክ በሀገር ውስጥ አቅምና ከውጭ በማስገባት  ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን በመጠቀም ለደንበኞቻችን ዘመናዊ የባንክ አገልግሎትን ማቅረቡን ቀጥሏል፡፡

ከነዚህ ስኬቶች በተጨማሪ ዘመን ባንክ በኢትዮጵያ ልዩ አገልግሎት በመስጠትና ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅ ረገድ ግንባር ቀደም ነው። ባንኩ ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር የንግድ ክፍያዎችን ለመክፈል የሚያገለግል ኤምፒጂኤስ የተባለ የኢኮሜርስ መድረክ በማስጀመር የመጀመሪያ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ የዘመን ባንክ የኮኦፕቲሽን ፅንሰሀሳብን በመጠቀም ከፊንቴክ እና ከክፍያ መሳሪያ አዘጋጆች ጋር በርካታ ስምምነቶችን ፈፅሟል። ይህ ስትራቴጂካዊ አቀራረብ ባንኩ በተናጥል ተደራሽ ያልሆኑ ገበያዎችን እንዲደርስ አስችሎታል