
ዘመን ባንክ ለግብረሰናይ ድርጅቶች 29.5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
ዘመን ባንክ ማኅበራዊ ሐላፊነቱን ለመወጣት ባለው ቁርጠኝነት በማኅበረሰብ አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ 19 ግብረሰናይ ድርጅቶች 29.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
ወ/ሮ እንዬ ቢምር የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢና አቶ ደረጀ ዘበነ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም በባንኩ ዋና መ/ቤት በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ ድጋፉን ለግብረሰናይ ድርጅቶቹ አስረክበዋል፡፡ የተሰጠው ድጋፍ እንደ ድርጅቶቹ የሥራ ስፋትና የሚሰጡት አገልግሎት ከአንድ ሚሊየን ብር እስከ ሁለት ሚሊየን ብር የሚደርስ ነው፡፡ ከእነዚህ መካከል አስራ አምስቱ አዲስ አበባ ሆነው አገልግሎታቸውን የሚሰጡ ሲሆን ቀሪዎቹ አራቱ በባህርዳር፣ መቀሌ፣ ሀዋሳና አዳማ ይገኛሉ፡፡
በዚህ ወቅት ወ/ሮ እንዬ ቢምር ባደረጉት ንግግር ዘመን ባንክ ባለፉት ዓመታት የተለያዩ ማኅበረሰብ ክፍሎችን የተሻለ ሕይወት እንዲኖራቸው ለማስቻል የሚረዱ ድጋፎችን በመስጠት ተቋማዊ ማኅበራዊ ሐላፊነቱን ሲወጣ መቆየቱን አስታውቀዋል፡፡ በተጨማሪም ባንኩ ይህንን መልካም ምግባር አጠናክሮ በመቀጠል ለግብረሰናይ ድርጅቶቹ ይደግፈል ብለዋል፡፡
ከዘመን ባንክ ድጋፍ የተደረገላቸው ግብረሰናይ ድርጅቶች መቄዶንያ በጎ አድራጎት ማኅበር፣ ሜሪ ጆይ፣ ዲቦራ ፋውንዴሽን፣ የኢትዮጵያ ካንሰር አሶሴሽን፣ ችልድረን ኸርት ፈንድ፣ ማቴዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ፣ ትኩረት ለሴቶችና ለህጻናት ማኅበር፣ ነህምያ ኦቲዝም ማዕከል፣ ጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃና ማገገሚያ ማዕከል፣ የወደቁትን አንሱ የነዳያን የበጎ አድራጎት ማኅበር፣ የኢትዮጵያ የኩላሊት ህመም ማኅበር፣ ፍሬምናጦስ የአረጋውያን፣ የአእምሮ ህሙማንና የህጻናት መርጃ ድርጅት፣ ቤተሰብ የበጎ አድራጎት ማኅበር፣ ቤቴል ችልድረንስ ሆም አሶሴሽን፣ ቤዛ ለህይወት የልማት ድርጅት፣ ክብር ለአረጋውያን፣ ርኆቦት ፊዲንግ ኤንድ ስተዲ ሴንተር፣ ህይወት ኢትዮጵያ እና ብራይት ወርልድ ብላይንድ ውሜን አሶሴሽን ናቸው፡፡
hashtag#ዘመንባንክ hashtag#corporatesocialresponsibility hashtag#donation hashtag#ZemenBank



